Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dob

Department of Buildings

DOB is excited to introduce Pop-Up Permits (PUPs), our new pilot program for customers to get a streamlined Certificate of Occupancy (C of O) for temporary use of a previously vacant building for up to one (1) year - all without going through the traditional permitting process to maximize the time the space can operate. Learn more about Pop-Up Permits (PUPs).

DOB
Menu Button
 

Welcome to the Department of Buildings

1 I Need To...
keyboard_arrow_right
2 ...
keyboard_arrow_right
3  

Amharic (አማርኛ)

This page contains information about the Department of Buildings (DOB) services for Amharic speakers.

የኮሉምቢያ ዲስትሪክት የግንባታ መመሪያ (Department of Buildings)

የኤጀንሲው ስም፡- የግንባታ መምሪያ

የኮሉምቢያ ዲስትሪክት የግንባታ መምሪያ ተልዕኮ የነዋሪዎችን፣ የንግድ ድርጅቶችንና ጎብኝዎችን ደኅንነት መጠበቅ እንዲሁም ፈቃድ በመስጠት፣ ቁጥጥሮችን በማድረግና ሕጎችን በማስፈጸም የአካባቢውን ልማት ማሳደግ ነው።

አገልግሎቶች

የግንባታ መምሪያው በኮሉምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ያለውን የግንባታ እንቅስቃሴ የመቆጣጠር ኃላፊነት አለበት። ኤጀንሲው የተጠናከረ የፈቃድ አሰጣጥ ሥራዎችን የሚመራ ሲሆን የግንባታ ደንቦችና የዞን መመሪያዎች መከበራቸውን ለማረጋገጥም ሁሉንም የግንባታ ሰነዶች ይገመግማል፡፡ በተጨማሪም የቁጥጥርና ክትትል ባለስልጣን ያለው ሲሆን በዚህ ባለሥልጣን በኩልም በሕጉ በተቀመጠው መሰረት የግንባታ ሥራዎች፣ የግንባታ ስርዓቶችና የኪራይ ቤቶች ቁጥጥር ይደረጋል፡፡

ክፍሎችና ኃላፊነቶች

የዳይሬክተር ጽ/ቤት

የዳይሬክተሩ ጽ/ቤት ተግባራት የሰው ኃይልን፣ የድጋፍ አገልግሎትን፣ የግዥና የውል አስተዳደርን፣ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራርን፣ የኤጀንሲውን የፋይናንስ ስራዎችና የመዝገብ አያያዝን ጨምሮ አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን፣ የኤጀንሲው የሥራ አፈፃፀምና የመረጃ አያያዝን፣ የደንበኞች አገልግሎትና የሒሳብ አስተዳደርን፣ የሕግ ጉዳዮችን፣ የሕዝብ ግንኙነቶች እና የመረጃ ቴክኖሎጂን ያካትታሉ፡፡

የኮንስትራክሽንና የግንባታ ደረጃዎች ጽ/ቤት

የኮንስትራክሽንና የግንባታ ደረጃዎች ጽ/ቤት ፈቃድ የመስጠት፣ የግንባታ ሥራዎች ደንቦችን በጠበቀ መንገድ መከናወናቸውን የማረጋገጥ፣ የግንባታ ፍተሻዎችን የማከናወን፣ የአረንጓዴ ግንባታዎች እና የሶስተኛ ወገን ፍተሻዎችን የማስፈፀም ኃላፊነት አለበት፡፡ ይህ ክፍል ለአደጋ እና ለአደጋ ምላሽ የግንባታና መዋቅር ግምገማዎችን የሚያካሒድ ሲሆን የመሐንዲስ ቢሮንም በውስጡ ይዟል። ይህ ክፍል የሚከተሉት ስድስት ተግባራት ይኖሩታል፡-

  • ፍቃድ አሰጣጥ፡- ለግንባታ ፍቃድና ለነዋሪነት ማረጋገጫ የዲስትሪክቱ ማዕከላዊ የማመልከቻ መቀበያና ማቅረቢያ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፤ የሕግ ተፈጻሚነትን ለማረጋገጥ የግንባታ ዕቅድ የቴክኒክ ግምገማዎችን ያከናውናል እንዲሁም የግንባታ ፈቃዶችን ያጸድቃል፣ ይሰጣል፡፡
  • የግንባታ ሕጎች፡- በዲሲ ምክር ቤት የተደነገጉትን ሕጎችና ደንቦችን ለመደገፍ ፖሊሲዎችን ያወጣል፣ ለግንባታ ሕጎች ማስተባበሪያ ቦርድ (CCCB) ግብዓቶችንና አስተዳደራዊ ድጋፎችን ይሰጣል እንዲሁም በዓለምአቀፉ የሕግ ም/ቤት ሞዴል ሕግጋት ውስጥ በተመለከተው መሰረት በቂ ለሆነና ደኅንነቱ ለተጠበቀ ግንባታ ያሉትን ወቅታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት በዲስትሪክቱ የግንባታና የንግድ ሕጎች ላይ ማሻሻያዎችን ያደርጋል፡፡
  • የግንባታ ቁጥጥር፡- የሕገ-ወጥ ግንባታ ቁጥጥርን ጨምሮ በፈቃድ ላይ የተመሰረተ ግንባታ የፍተሻ ጥያቄዎችን ያስተናግዳል፣ የዲስትሪክቱ የግንባታ ደንቦችና የዞን መመሪያዎች መከበራቸውን ለማረጋገጥ ተገቢ መመሪያዎችንና ማሳወቂያዎችን ይሰጣል እንዲሁም ከሃገር ውስጥ የደኅንነትና የአደጋ ሥራ አመራር ኤጀንሲ ጋር በመቀናጀት የኢ.ኤስ.ኤፍ14 የአደጋና የአደጋ ምላሽ አሰጣጥ መስፈርቶችን የሚደግፉ ድንገተኛ የግንባታ አደጋዎችን የሚመለከቱ ግምገማዎችን ያከናውናል።
  • አረንጓዴ ግንባታ፡- የአረንጓዴ ግንባታ ሕግን፣ የአረንጓዴ ኮንስትራክሽን ሕግንና የኢነርጂ ቁጠባ ሕግን ጨምሮ በአረንጓዴ ሕግ ደንቦች ስር ያሉ በኮሉምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የሚከናወኑ ግንባታዎችን ይቆጣጠራል። ሥራው በግንባታ መመሪያው የፍቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ተግባራት ውስጥ የሚከናወን ሲሆን ይህም የግንባታ ሰነዶችን መገምገምን፣ የግንባታ ምርመራዎች ማካሔድን እንዲሁም የኮሉምቢያ ዲስትሪክትን ይበልጥ ዘላቂና አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለመገንባት የሚደረጉ ጥረቶችን አጠናክሮ ለመቀጠል ከእህት ኤጀንሲዎች፣ ከግንባታ ኢንዱስትሪውና ከማኅበረሰቡ ጋር መቀናጀትን ያካትታል።
  • ቀያሽ፡- በኮሉምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የሚገኙትን ሁሉንም የመሬት ይዞታዎች እንዲሁም የግልና የዲስትሪክት የመንግስት ንብረት ክፍሎችን ሕጋዊ መዛግብት ያዘጋጃል፣ ይይዛል፤ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ምዝገባን ያካሂዳል እንዲሁም የፍተሻ ማረጋገጫዎችን ያከናውናል፡፡
  • የሶስተኛ ወገን ምርመራዎች፡- ብቃትና ማረጋገጫ ያላቸው መንግሥታዊ ያልሆኑ ሰዎች ወይም አካላት መደበኛና ልዩ ምርመራዎችን እንዲያካሂዱ፣ የሚከናወኑት ሥራዎች የኮሉምቢያ ዲስትሪክት የኮንስትራክሽን ደንቦችን የተከተሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ግምገማዎችን እንዲያቅዱ ፍቃድ ይሰጣቸዋል። ተቀባይነት ያለው የሶስተኛ ወገን የእቅድ ግምገማን እና ተቆጣጣሪ ተቋማትና በበላይነት ይቆጣጠራል፤ ለእያንዳንዳቸው ተግባራት የፖሊሲ መመሪያዎችን ያዘጋጃል፣ ያስፈጽማል፤ በዲስትሪክቱ ውስጥ የማሞቂያ (ቦይለር) እና የአሳንሰር (ሊፍት) ገጠማዎችን ይፈትሻል፣ ይቆጣጠራል።

የስትራቴጂ ሕግ ማስፈጸሚያ ቢሮ

የስትራቴጂ ሕግ ማስፈጸሚያ ቢሮው ለሕግ አፈጻጸም፣ ለሕግ ጥሰቶች እንዲሁም ለገንዘብ ቅጣት አወሳሰኖች ኃላፊነት አለበት። ይህ ክፍል የማስፈጸሚያ ስልቶችንና አሰራሮችን ያዘጋጃል፣ ይተገበራል፣ ጥሰቶችን ይቆጣጠራል፣ የገንዘብ መቀጮዎችን ያስፈጽማል እንዲሁም የነዚህን የሁለቱን ሒደትና የሌሎች ተግባራት ያሉበትን ሁኔታ ይከታተላል፡፡ ይህ ክፍል የቅነሳ (abatement) ማረጋገጫ ሲቀርብ ከፍርድ ቤት ውጭ ያሉ የሲቪል ጥሰቶችን ለመፍታት አማራጮችን ያቀርባል። በተጨማሪም ቢሮው የሚከተሉትን ሁለት ተግባራት በሥሩ ይዟል፡-

  • ሕግ አስፈጻሚ፡- የማስፈጸሚያ ስልቶችንና አሰራሮችን ያዘጋጃል፣ ይተገበራል፡፡
  • የሲቪል ጥሰቶችና የቅጣቶች አወሳሰን፡- ሁሉንም የሲቪል ጥሰቶች ከአስተዳደር ችሎት ቢሮ ጋር በመቀናጀት ይመለከታል፣ ቅጣቶችን ይሰበስባል እንዲሁም የንብረት እገዳዎችን ባልተከፈሉ ቅጣቶች ላይ ያስቀምጣል፡፡

የመኖሪያ ቤቶች ቁጥጥር ቢሮ

የመኖሪያ ቤቶች ቁጥጥር ቢሮ ባዶና የተበላሹ ንብረቶችን የመፈተሽና የመለየት፣ የኪራይ ቤቶች ፍተሻዎችን የማካሄድ፣ በቅነሳና በሕግ ማስፈጸም ተግባራት አማካኝነት የቤቶችን ደኅንነት የማሳደግ ኃላፊነት አለበት። ቢሮው የሚከተሉት ሶስት ተግባራት ይኖሩታል፡-

  • ባዶና የተበላሹ ንብረቶች፡- በኮሉምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ያሉ ክፍት ንብረቶችን ይመዘግባል፣ ከቀረጥ ነፃ ለሚደረጉ ባዶ ንብረቶች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ያዘጋጃል፣ የባዶ ንብረቶች የጥገና ስታንዳርዶችንና ምዝገባን ማሟላታቸውን ለማረጋገጥ ባዶና የተበላሹ ንብረቶችን ይፈትሻል እንዲሁም የግብር ምደባ ለማከናወን ተግባር ይረዳ ዘንድ የነዋሪነት ሁኔታን ለግብርና ገቢዎች ቢሮ ያሳውቃል።
  • የኪራይ ቤቶች ፍተሻ፡- የመኖሪያ ቤቶችን ይመረምራል እንዲሁም የቤቶች መመሪያ ጥሰትን የሚመለከቱ ማሳወቂያዎችን ይሰጣል፡፡
  • የመኖሪያ ቤቶች እድሳት፡- የንብረት ጥገና ደንቦችን ጥሰቶች ያስወግዳል፣ የቅነሳ ውሎችን ያስተዳድራል እንዲሁም ላልተከፈሉ የቅነሳ ወጪዎች ልዩ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል፡፡

የዞን አስተዳደር ቢሮ

የዞን አስተዳደር ቢሮው የዞን ደንቦችን የመምራትና የመወሰን ኃላፊነት አለበት።

የትርጉም አገልግሎቶች

በቋንቋዎ እርዳታ ለማግኘት እባክዎን በ(202) 671-3500 ቢሮአችንን ያነጋግሩ። ወደ ቢሮአችን ሲደውሉ ወይም ቢሮአችንን ሲጎበኙ፣ ከአስተርጓሚ ጋር የሚያገናኝዎት ሰራተኛ ያገኛሉ።

 

አድራሻ፡-

የግንባታ መምሪያ

1100፣ 4ኛ መንገድ ኤስ.ደብሊው

ዋሽንግተን፣ ዲሲ 20024

የስልክ ቁ.፡- 202-671-4300

dob.dc.gov